በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት ጌሾ ወንዝ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ 18 ሰው የጫነ ሚኒባስ ታክሲ ዋናውን መንገድ ስቶ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ በተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ 18 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጎጂዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ እና በፖሊስ አምቡላንስ ወደ አቤት ሆስፒታልና አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።
ለኮሚሽኑ የአደጋ ጥሪ እንደደረሰ የአምቡላንስ አገልግሎት ቡድኑ በስፍራው በመገኘት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በህይወት በማውጣትና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በመስጠት ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አድርጓል።
ጉዳት ከደረሰባቸዉ ተግጂዎች መካከል አንድ ነፍሰ ጡር ሴት እና ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች ይገኙበታል።
የአደጋዉን መንስዔ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ፖሊስ እያጠራ እንደሚገኝ የእሳትናአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።