የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱ በሁሉም አካባቢዎች በተሳካ መልኩ እየተካሄደ ነው – ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)

You are currently viewing የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱ በሁሉም አካባቢዎች በተሳካ መልኩ እየተካሄደ ነው – ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም

የኢትዮዽያን መሰረታዊ ችግሮችን በንግግርና መግባባት ለመፍታት በሚያስችል ሁኔታ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱ በተሳካ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገለጹ።

በምክክር ሂደቱ እስካሁን አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት መከናወኑንም አመለክተዋል፡፡

በምክክሩም ሁሉም አጀንዳውን በነፃነት ያቀረቡበት አሳታፊ አውድ መፈጠሩን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በቅርቡ የተደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት በስኬት መጠናቀቁንም አስታውሰዋል።

በቀጣይ በትግራይ ክልል ምክክሩን በላቀ ስኬት ለማካሄድ የሚያስችል ተሞክሮ የተሰነቀበት በመሆኑ በዚሁ መሰረት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review