የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 ይካሄዳል

You are currently viewing የታዎቂ ሰዎች ስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 ይካሄዳል

AMN- ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያና ኢድቨርታይዚግ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የታዎቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሚያዚያ 23 እና 26 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

ሁለቱ ተቋማት ዛሬ በሀርመኒ ሆቴል ፌስቲቫሉን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫውም በፌስቲቫሉ በታዎቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃዊያን እና ቲክቶከሮች መካከል የእግር ኳስ ውድድርን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ፌስቲቫሉ በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ቢሪሞ ሜዳ እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ሚያዚያ 23 በጥሎ ማለፍ ውድድር ድምፃዊያን ከአርቲስቶች እንዲሁም ጋዜጠኞች ከቲክቶከሮች የእግር ኳስ ጨዋታ በማካሄድ የሁለቱ አሸናፊ ቡድኖች ሚያዚያ 26 ለፍፃሜ ጨዋታ እንደሚፋለሙ ተመላክቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መሀሪ ተመስገን፣ የፌስቲቫሉ ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከ1300 በላይ ዘመናዊ፣ ምቹ፣ ሳቢና አለምአቀፍ ስታዳርዳቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውንም አስታውሰዋል፡፡

የቅዳሜ ሚዲያና አድቨርታይዚግ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ አዳነ አረጋ፣ ፌስቲቫሉ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከፌስቲቫሉ የሚሰበሰብ ገንዘብ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአአምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እንደሚውል የቢሮው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review