የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተጀመረ

You are currently viewing የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተጀመረ

AMN-ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የሰራተኞች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በድምቀት ተጀምሯል።

በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ በተከናወነው መርሐ ግብር በርካታ የተቋሙ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከሰራተኛው ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርገዋል።

አቶ ካሳሁን ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ የሰራተኛውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል በመሆኑ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በስፖርታዊ ፌስቲቫሉ በዛሬው ዕለት የእግርኳስ ውድድሮች ተከናውነዋል። በቀጣይም የሩጫ ፣ ቮሊቦል እና የገመድ ጉተታ ውድድሮች እንደሚከናወኑ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review