የጥራት መንደሩ የኢትዮጵያ ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንዲጨምር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው -ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶር)

You are currently viewing የጥራት መንደሩ የኢትዮጵያ ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንዲጨምር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው -ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶር)

AMN – ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም

የጥራት መንደሩ መገንባት የኢትዮጵያ ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንዲጨምር በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ።

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት መንደር መገንባት የተቀናጀና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት ማስቻሉንም ተጠቅሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላትን የጥራት መንደር ባለፈው ህዳር ወር 2017 ዓ.ም መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የጥራት መንደር የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣንን የያዘ ነው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የጥራት መንደሩ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በብዛት የማይገኙ የሴራሚክ፣ የባትሪ እና የሶላር ሀይል ማመንጫ መሳሪያዎችን መፈተሽ የሚያስችሉ ላቦራቶሪዎችን ጭምር ያካተተ ነው፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፉን የጥራት መንደር መገንባቷን ነው ያነሱት፡፡

የጥራት መንደሩ በመገንባቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሰራር ስርዓቶች በመዘርጋት በአለም አቀፍ ደረጃ የነበረንን ተቀባይነት እንዲጨምር የሚያስችል እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review