ኢትዮጵያ አካታች የኢንዱስትሪ ልማትና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ አካታች የኢንዱስትሪ ልማትና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው
  • Post category:ልማት

AMN- ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ አካታች የኢንዱስትሪ ልማት እና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ እየሰራች እንደምትገኝ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ ገለጹ።

3ተኛው የኢራን-አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ኮንፈረንስ በቴህራን እየተካሄደ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ “ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ፣ ኢትዮጵያ አካታች የኢንዲስትሪ ልማትን ለማምጣትና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ እያከናወነች ያለውን የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች በሚመለከት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፣ ተሞክሮዎችንም አጋርተዋል።

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚና የፖሊሲ ማሻሻያ አማካኝነት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማበረታቻ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አጠቃላይ የንግድ፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት አካባቢዎችን ለማሻሻልና ለዘርፉ ተዋናዮች ምቹ ለማድረግ በቁርጠኝት እየሰራ እንደሚገኝ ማመላከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለውጭ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ሳቢ የንግድና ኢንቨስትምንት ሁኔታ ለመፍጠር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የገንዘብ ፖሊሲ፣ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት እና ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ነው ያብራሩት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review