በቴክኖሎጂ የጎለበተች አፍሪካን በጋራ ለመምራት ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 ጉባኤ የላቀ ድርሻ አለው- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

You are currently viewing በቴክኖሎጂ የጎለበተች አፍሪካን በጋራ ለመምራት ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 ጉባኤ የላቀ ድርሻ አለው- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም

በቴክኖሎጂ የጎለበተች አፍሪካን በጋራ ለመምራት ኢኖቬሽን አፍሪካ (Innovation Africa) 2025 ጉባኤ የላቀ ድርሻ እንዳለው በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለፁ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴርና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት April 28 – 30/2025 እየተካሄደ የሚገኘው የኢኖቬሽን አፍሪካ (Innovation Africa) 2025 መድረክ የሁለተኛ ቀን ፕሮግራም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኢኮኖሚን በአፍሪካ ለማጎልበት የሚያስችል አለማቀፋዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው በአፍሪካዊያን ትብብር የዲጂታል ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ እድገትን በማጎልበት በዓለም ተወዳዳሪ ለመሆነና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዓለማችን እውቀት የልማት ምንዛሪ በሆነበት ዘመን ወጣቶቻችንን የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትን ማስታጠቅ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ብለዋል።

በአህጉሪቱ ውስጥ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂን የሚያጎለብት ትብብርን ለማስፋት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቁርጠኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ በመደመር፣ በማብቃት እና በዘላቂነት ልማት የምትታወቀውን አፍሪካን የተሻለ የወደፊት ሁኔታ ለመገንባት እንተባበር ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review