አሜሪካ ቻይና ላይ በጣለችው የ145 በመቶ ታሪፍ ዙሪያ ለመነጋገር ፍላጎት እንዳላት የቻይና መንግስት ሚዲያ መግለጹ ተነግሯል፡፡
ከቻይና የመንግስት ሚዲያ ጋር ግንኙነት ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ አወጣው የተባለው መረጃ፣ ቤጂንግ በሯን ለድርድር ክፍት ማድረጓን ያሳየ መሆኑ ተመላክቷል።
ዩዩዋን ታንቲያን የተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ በይፋዊ ድረ ገፁ ባሰፈረው መረጃ፣ አሜሪካ በታሪፍ ጉዳይ ላይ ውይይት ለማድረግ በማሰብ በበርካታ መንገዶች ወደ ቻይና እየቀረበች እንደሆነ መግለጹን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት እና የኋይት ሀውስ የኢኮኖሚ አማካሪ ኬቨን ሃሴትን ጨምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናት የንግድ ውጥረቶችን ለማርገብ መሻሻሎች እንደሚኖሩ ተስፋ ማድረጋቸው ተመላክቷል።
የኢኮኖሚ አማካሪው ሃሴት ለሲ ኤን ቢ ሲ እንደተናገሩት፣ ታሪፍን በተመለከተ በሁለቱም መንግስታት መካከል ቀለል ያሉ ውይይቶች እንደነበሩ በማንሳት፣ ቻይና ባለፈው ሳምንት በአንዳንድ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የጣለችውን ቀረጥ ማቃለሏም የዚሁ መሻሻል ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።
በታምራት ቢሻው