84ኛው የዐርበኞች (የድል) በዓል እየተከበረ ነው

You are currently viewing 84ኛው የዐርበኞች (የድል) በዓል እየተከበረ ነው

AMN-ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም

84ኛው የዐርበኞች (የድል) በዓል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት በሚገኝበት ስፍራ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዐሉ ላይ አባት አርበኞች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉ አባት አርበኞች ድሉ የፀና የሀገር ፍቅር እና ከልብ የመነጨ የህዝብ ክብር የሚዘከርበት ነው ብለዋል፡፡

አሁን ያለው ትውልድ ፅናት እና አንድነትን ከትናንት አባቶች ሊወርስ ይገባልም ብለዋል፡፡

ትውልዱ አሁን ባለበት አውድ ድህነትን ድል የሚነሳ ሰላም እና አብሮነትንም የሚያፀና በመሆን የራሱን የአርበኝነት ታሪክ በደማቅ ቀለም ሊፅፍ ይገባል ሲሉ አባት አርበኞች ተናግረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review