ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “መዳረሻዎን ኢትዮጵያ ያድርጉ፤ ቆይታዎን ያራዝሙ” ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “መዳረሻዎን ኢትዮጵያ ያድርጉ፤ ቆይታዎን ያራዝሙ” ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ

AMN- ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “መዳረሻዎን ኢትዮጵያ ያድርጉ፤ ቆይታዎን ያራዝሙ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል እንደመሆኗ ልዩ የሆነ የንግድ እና የባህል መጎልበት ዕድል የምትሰጥ በአህጉራዊ ጉዳዮች በግንባር ቀደምትነት የምትቆም ሀገር ናት ብለዋል።

በእንከን የለሹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ወደ ጠበቀ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱ አስደሳች እንደሆነም ጠቁመዋል።

ዘመናዊ የመሰብሰቢያ ቦታዎች፣ ጥራት ያላቸው ማረፊያዎች እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ መሠረተ ልማቶች ያሏት ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ መሆኗንም አመላክተዋል።

ደማቅ ባህሏ፣ የባህል ምግቦቿ፣ ሙዚቃዋ እና አስደናቂ የተፈጥሮ ውበቷን ሲያክሉ፣ የመጨረሻውን የማይስ ቱሪዝም መድረሻዎን አግኝተዋል ማለት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

“መዳረሻዎን ኢትዮጵያ ያድርጉ፤ ቆይታዎን ያራዝሙ” በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review