
AMN – ግንቦት 6/2017 ዓ.ም
በመዲናዋ የትራንስፖርት ፍሰቱ የተፋጠነ እንዲሆን ለአውቶቡስ ብቻ የተፈቀደ መንገድ ቢኖርም ሌሎች ተሽከርካሪዎችም ስለሚጠቀሙበት ፍጥነቱ የተገደበ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡
የቢሮው ጥናትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96.3 ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ ለብዙሃን ትራንስፖርት በተፈቀደው መንገድ የመንግስት መስሪያቤት መኪኖች፣ የፀጥታ አካላትና የዲፕሎማት ተሽከርካሪዎች ስለሚጠቀሙበት በተፈለገው ልክ ግቡን አልመታም።
በመሆኑም በቀጣይ ለብዙሃን ትራንስፖርት በተሠራው መንገድ ላይ ከአንቡላንስ ውጭ ሌሎች ተሽከርከሪዎች እንዳይጠቀሙ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ምክትል ቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
በሲሳይ ንብረቱ