በክሮሺያ ዛግሬብ በተደረገው ኮንቲኔንታል ቱር አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጥሩ ውጤት አምጥተዋል።
በሴቶች 1500 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር አሸንፋለች።
ጉዳፍ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3:58.14 የሆነ ሰዓት ወስዶባታል ።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ብርቄ ኃየሎም በ3:59.19 ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ሳምራዊት ሙሉጌታ ደግሞ ስድስተኛ መውጣት ችላለች።
በሌላ ውድድር በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ቢኒያም መሀሪ በ13:03.57 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሸዋንግዛው ግርማ