የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከሽልማት ምን ያህል ገንዘብ ያገኛሉ?

AMN-ግንቦት 19/2017 ዓ.ም

ባሳለፍነው እሁድ የተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለተሳታፊ ክለቦቹ ጠቀም ያለ የሽልማት ገንዘብ ይሰጣል።

አትሌቲክ እንደዘገበው ከሆነ ግምታዊ የሽልማት ገንዘቡ ከፍተኛው 181.5 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅተኛው ደግሞ 110.9 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚደርስ ዘግቧል።

ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ከፍተኛ የሽልማት ገንዘብ በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል። የመርሲሳይዱ ክለብ በውድድር ዓመቱ ለነበረው ተሳትፎ 181.5 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ካዝናው ከቷል።

አርሰናል 177.8 ሚ.ፓ ሁለተኛ ደረጃ ሲቀመጥ ማንችስተር ሲቲ 171.5 ሚ.ፓ በማግኘት ይከተላል።

በሽልማት ገቢው ማንችስተር ዩናይትድ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቶትንሃም ሆትስፐርስ 16ኛ ደረጃ ይዟል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review