ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሃገሪቱ የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታ የመስክ ላይ ግምገማ ማድረጋቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሃገሪቱ የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታ የመስክ ላይ ግምገማ ማድረጋቸዉን ገለጹ

AMN- ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአይነቱ ልዩ፣ ለሀገራችን የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታን የመስክ ላይ ግምገማ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በመሀል አራዳ ከታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር ተሰናስሎ 3 ግዙፍ እና ዘመናዊ ሞሎች፣ አፓርትመንቶች ከአራዳ ፓርክ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተናበው አካባቢውን ሁሉ አስውበው መንፈሳችንን ሊያድሱ፣ ኢኮኖሚያችንን ሊያነቃቁ፣ ሰፊ የስራ እድል ሊፈጥሩ እና ተወዳዳሪ ሊያደርጉን በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የአራዳ ሌግዠሪ ሞል፣ አዲስ ግራንድ ሞል እና ኦሊ ሞል ሶስቱ የሀገራችንን የግብይት ክፍተት የሚዘጉት ሞሎች በከተማ አስተዳደሩ እና የግል ሴክተር አጋርነት እየተገነቡ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ከነዚህ ዉስጥ ዛሬ በአይነቱ ልዩ፣ ለሀገራችን የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታን የመስክ ላይ ግምገማ አድድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።

ባደረግነው ግምገማም ግንባታው ከተጀመረ ገና 10 ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም ስራው በጥራትና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወነ መሆኑን ተገንዝበናል ነው ያሉት።

ግንባታው ሲጠናቀቅ የከተማችንን ገቢ ለማሳደግ፣ የስራ ዕድልን ለመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘት እና ሁሉን አይነት ግብይት ከአንድ ስፍራ ማከናወን የሚያስችል እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያሟላ በመሆኑ ያለው ፋይዳ የጎላ ይሆናል ሲሉም አክለዋል።

አዲስ አሰራርን በመቀበል እና “አብሮ ሰርቶ ውጤታማ መሆን ይቻላል” ብለው በማመን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በአጋርነት አብረው እየሰሩ ላሉ የግል ሴክተሮችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review