“አንድ ጠርሙስ ቀዝቃዛ አየር በአምስት ዶላር እየተቸበቸበ ነው” ሲል የዓለማችን ድንቃ ድንቅ ወሬዎች ምንጭ የሆነው ኦዲቲ ሴንትራል እ.ኤ.አ ነሐሴ 25 ቀን 2022 ያወጣው ዘገባ ዓለምን ያነጋገረ ነበር፡፡
እንደ ኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ከሆነ ከኮሎምቢያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው መዴሊን ወደ ኮሎምቢያ የመጣው ወጣት ሥራ ፈጣሪ ሁዋን ካርሎስ አልቫራዶ የትውልድ ከተማውን አየር በጠርሙስ አሽጎ በመሸጥ በቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እንደሚያገኝ ተናግሯል።
ተፈጥሮ ነፋሻ አየሯን እንደ እርጎ እያጠጣች ያሳደገቻት ሜዴሊን “የዘላለም ጸደይ ከተማ” ተብላም ትታወቃለች። ዓመቱን በሙሉ ነፍስን ከስጋ የሚያስታርቅ ደስ የሚል የአየር ጠባይ የታደለች ከተማ ናት፡፡ ከዚች ከተማ ብዙም ሳይጓዙ ያ! በመንፈስ የሚገመጥ፤ በልብ የሚደመጥ አየር አይገኝም፡፡
ይህንን የተረዳው ወጣቱ ስራ ፈጣሪ ሁዋን ካርሎስ አልቫራዶ የራሱን የአየር ሽያጭ ንግድ ጀመረ፡፡ ይህ የታሸገ አየር (Medellin Air) የሚል ስያሜ የተሰጠው የወጣቱ ፈጠራ በየማህበራዊ ሚዲያውም ሆነ በኮሎምቢያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰርክ ቢነገርም የማይሰለች ዜና ሆኗል፡፡
አዎ! ምድራችን፡- አየሯ ሳይቀር እንደ እርጎ የሚማግ እንደ ዳቦ የሚገመጥ ፀጋን የታደለች ማዕድ ናት፡፡ በዝናብ አብቅላ በፀሐይ አብስላ ሕይወት ያለውን ሁሉ ትመግበዋለችና፡፡
ግና ሕይወት ያለው ሁሉ የምድርን በረከት በአግባቡ ካልጠበቀ የሰማዩ ጠል ምድርን ማረስረሱ፣ አየሩም ስጋና መንፈስን ማደሱ ዘበት ይሆናል፡፡ አበው “አንድም ለበረከት አንዳንዴም ለመቅሰፍት” እንዲሉ።“ዝናቡ ዘነበ ወንዙ ሞላልሽ
እንግዲህ ያገር ልጅ ማር ትበያለሽ” ማለቱ ይቀርና የሰማዩ ዝናብ አሲድ ሆኖ ይመጣል። ዓለማችን በታሪኳ ይህንን እውነት በተለያዩ ጊዜያት መዝግባለች፡፡
የባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ በአኒታ ሲንግ እና ማድሆሊካ አግራዋል የአሲድ ዝናብ እና የስነ ምህዳር ውጤቶች “Acid rain and its ecological consequences” በሚል ርዕስ ያደረጉትን ጥናት ዋቢ አድርጎ እ.ኤ.አ 2008 ይፋ እንዳደረገው እ.ኤ.አ በ1852 ስኮትላንዳዊው ኬሚስት ሮበርት አንገስ ስሚዝ በእንግሊዝና በስኮትላንድ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች የዝናብ ውሃን ሲያጠና “የአሲድ ዝናብ” ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሉን ተጠቅሞበታል።
በተለይም እ.ኤ.አ በ1872 ዓ.ም የታተመው የኬሚስት ሮበርት አንገስ ስሚዝ አየር እና ዝናብ “Air and Rain” የተሰኘው መጽሐፍ የአሲድ ዝናብ ምንነትና የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ዓለም በሚገባ እንድትረዳው አድርጓል፡፡ ስለ ካርቦን ሽያጭም አዲስ እሳቤን አፍልቋል።
የአሲድ ዝናብ የአፈር አሲዳማነትን ከፍ ስለሚያደርገው ምድር ማር የሆነው ምርቷ ወደ መርዛማነት እንዲቀየር፣ የውሃ አካላትና በውስጣቸው የሚኖሩ ፍጡራን ሁሉ አንዲሞቱ አሊያም ጎጅ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በጥቅሉ የምድርን በረከት ወደ መርገምትነት ይቀይረዋል፤ ይላል የባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፡፡
የአሲድ ዝናብ ታሪክ ቀደም ሲል በእንግሊዝና በስኮትላንድ የተከሰተ ሀቅ ቢሆንም ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ይህንንም ተከትሎ ለካርቦን ሽያጭ ትኩረት እንድትሰጥ ያደረጋት ክስተት የተፈጠረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በአሜሪካ ምድር የወረደው የአሲዳማ ዝናብ ታሪክ ነው፡፡
በወቅቱ በአሜሪካ ያሉ ፋብሪካዎች እና የኃይል ማመንጫዎች እየተስፋፉ ሲሄዱ ከፍተኛ መጠን ያለው ሰልፈር ዳይ ኦክሳይድ (SO2) እና ናይትሮጅን ኦክሳይድ (NOx) ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ ጀምረው ነበር፡፡
በዚህ ምክንያት በአሜሪካ ግዛቶች ለበረከት ሳይሆን ለጥፋት የወረደው የአሲድ ዝናብ ያስከተለው መዘዝ የችግሩን አሳሳቢነት ፍንትው አድርጎ ለዓለማችን ሀያላን ሀገራት አሳዬ፡፡
ይህንንም ተከትሎ የዓለም ሀገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደው የአካባቢ ስጋት እና በየሀገራቱ እያንዣበበ ያለውን የአሲድ ዝናብ ለመቋቋም ተባብረዋል። በተለይም፣ ዩናይትድ ስቴትስ እ.ኤ.አ በ1990 የንፁህ አየር ህግ ማሻሻያ ላይ የተመሰረተውን የአሲድ ዝናብ ፕሮግራም (ኤ አር ፒ) ተግባራዊ ለማድረግ ተገደደች፡፡
በሌላ በኩልም እ.ኤ.አ በ1999 በአውሮፓ ህብረት የፀደቀው የጎተንበርግ ፕሮቶኮል በሰልፈር ዳይ ኦክሳይድ፣ ናይትሮጅን ኦክሳይድ፣ አሞኒያ እና ተለዋዋጭ ኦርጋኒክ ውህዶች ላይ ያነጣጠረ ነበር።
የወጡትን ዓለም አቀፍ ህጎች ተከትሎ ቀላል የማይባሉ ሀገራት በኃይል ማመንጫዎቻቸው ከተፈጥሮ የተስማሙ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመዋል። ኢንዱስትሪዎች የበካይ ልቀቶችን ለመቀነስ የተለያየ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ ዛሬ ላይ የ SO2 እና NOx ደረጃዎች እ.ኤ.አ ከ 1980 ከነበሩበት ደረጃዎች በግማሽ መቀነስ ችሏል፡፡ ለዚህ ለውጥ ደግሞ የካርቦን ንግድ ያለው ድርሻ የሚናቅ አይደለም ይላል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው የቅርብ ጊዜ መረጃ፡፡
ካርበን ንግድ የብክለት መጠናቸውን ለሚቀንሱ ኩባንያዎች ማበረታቻ በማድረግ ብክለትን መቆጣጠር የሚያስችል የገበያ ስርዓት ነው፡፡ ኩባንያዎች እንደ ደን ልማት ወይም የታዳሽ ኃይልን በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ብድር የሚያገኙበትም አንዱ መንገድ ነው።
ዓለም አቀፍ የካርቦን ትሬዲንግ “International carbon trading” ሀገራት የተፈቀደላቸውን የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን በመሸጥ ወይም በመግዛት ብሔራዊ የልቀት ቅነሳ ግባቸውን የሚያሳኩበት በቶኪዮ ፕሮቶኮል የተዋወቀ ጽንሰ ሀሳብ ነው። የካርቦን ንግድ ዓለም አቀፍ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል መንገድ ተደርጎም ይወሰዳል።
የካርበን ክሬዲት ግዙፍ ኩባንያዎች እስከ 1 ቶን ካርበን ዳይ ኦክሳይድ እንዲለቁ ይፈቅዳል፤ ቀስ በቀስ ልቀታቸውን እንዲቀንሱና የሚለቁትን ካርበን ከከባቢ አየር ላይ እንዲያስወግዱም ያሳስባል። የካርበን ክሬዲት ተጠቃሚዎች በታዳጊ ሀገራት የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ለማገዝ የሚውል መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ እንዲያደርጉም ይጠበቃል፡፡
ዋና መቀመጫዋን ከብሪቲሽ ደሴቶች አንዷ በሆነችው ዳግላስ ያደረገችው ዕለታዊና ሳምንታዊ የምርምር ጋዜጣ “ሳይንስ X” በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈው የደን የካርቦን ክሬዲት መርሐ ግብርን አስመልክቶ እ.ኤ.አ ነሀሴ 27 ቀን 2023 ይፋ ባደረገችው ጥናታዊ መረጃ መሰረት መርሐ ግብሩ በአንድ በኩል ጥሩ በሌላ በኩል ስጋት ያለበት ነው። ጥናቱ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ታንዛኒያ፣ ኮሎምቢያ፣ ካምቦዲያ እና ፔሩ በመንግስታቱ ድርጅት የሬድ ፕላስ ፕሮግራም የሚደገፉ 18 የካርበን ክሬዲት ፕሮጀክቶችን ዳስሷል።
በጥናቱ የተካተቱትና የከባቢ አየር ብክለትን ይቀንሳሉ የተባሉት ፕሮጀክቶች የደን መጨፍጨፍን በመቀነስ ረገድ ያከናወኑት ስራ ከሚጠበቅባቸው ከ6 በመቶ አይበልጥም፡፡ ይህም የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያሳይ እንደሆነ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
ዋና መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው “Green Match.co.uk.” ዓለም አቀፍ የካርበን ልቀትን አስመልክቶ “Countries with the Highest Carbon Foot print 2025” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በአካባቢና በሰው ልጆች ጤና ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ ተፅዕኖ በሚያሳድረው ካርበን ዳይ ኦክሳይድ (CO2) ልቀት መጠናቸው፡- ቻይና፣ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ጃፓን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራን፣ ጀርመን፣ ሳውዲ አረቢያ እና ደቡብ ኮሪያ በቀዳሚነት ተቀምጠዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በብሔራዊ ካርቦን ግብይት ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አካታችነትን፣ ተጠያቂነትንና ዘላቂ ልማት ማስፋፋት ላይ መሰረት ያደረገ የካርቦን ግብይት ዕድሎችን ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት አላት፡፡
ይህንንም ተከትሎ ለሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ተቀርፆ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተወሰደ ነው ያለው የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ለአብነትም የአረንጓዴ አሻራ፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ እቅድ፣ የታዳሽ ኃይል ልማትና የኤሌክትሪክ ፕሮግራም፣ የሞተር አልባ ተሽከርካሪ ኢኒሼቲቭና ሌሎች ስራዎችን በማሳያነት ጠቅሷል፡፡
እንደሀገር በአረንጓዴ ልማት ላይ እየተመዘገቡ ያሉ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ተከትሎ ኢትዮጵያ የካርበን ሽያጭ ስምምነት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጋር እያደረገች ነው፡፡ ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኖርዌይ ጋር የ75 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካርበን ሽያጭ ስምምነት ተፈራርማለች፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 2027 ድረስ የሚቆየው ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ ዘላቂነት ባለው በአረንጓዴ ደን ልማት ላይ ውጤታማ እየሆነች መምጣቷን ማሳያ እንደሆነም የደን ልማት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
የሰው ልጅ ንፁህ ውሃን እንደ ወተት እየጠጣ፣ ንፁህ አየርን እንደ እርጎ እየማገ፣ ከማጀቱ እንጀራ፣ ከጓሮው ሸንኮራን መብላት ካማረው፣ምድር የተሰጣትን ፀጋ ከነጣዕሙ መጠቀም ካሻው ሳይውል ሳያድር ተፈጥሮን መንከባከብ ግድ ይለዋል፡፡

በመለሰ ተሰጋ