አሜሪካ ከአዲሱ ድርድር በፊት ተጨማሪ ጥቃቶችን ማስወገድ አለባት ሲሉ የኢራኑ ሚኒስትር ተናገሩ

You are currently viewing አሜሪካ ከአዲሱ ድርድር በፊት ተጨማሪ ጥቃቶችን ማስወገድ አለባት ሲሉ የኢራኑ ሚኒስትር ተናገሩ

AMN – ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

አሜሪካ ከአዲሱ ድርድር በፊት ተጨማሪ የአየር ጥቃቶችን ከማድረስ መቆጠብ አለባት ሲሉ የኢራኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።

የኢራኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ ታኽት-ራቫንቺ የትራምፕ አስተዳደር ለኢራን በአሸማጋዮች በኩል ወደ ድርድር መመለስ እንደሚፈልጉ ቢነገራትም ንግግሮች እየተካሄዱ ባለበት ወቅት በጣም አስፈላጊ በሆነው ጥያቄ እና በተጨማሪ ጥቃቶች ላይ አቋማቸውን ግልጽ አላደረጉም ብለዋል።

የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የጀመረው በፈረንጆቹ ሰኔ 13 ወር ሲሆን ጥቃቱም ከሁለት ቀናት በኋላ በሙስካት ሊካሄድ የነበረውን ስድስተኛ ዙር ቀጥተኛ ያልሆነን የኒውክሌር ንግግር አፍርሷል ሲሉ የወነጀሉ ሲሆን አሜሪካም የአየር ጥቃቱን በመቀላቀል ሶስት የኢራን የኒዉክለር መሰረተልማቶች፣ ፎርዶን፣ ናታንዚን እና ኢስፋሃንን በቦምቦች መደብደቧን አስታውሰዋል።

በዚህም እስራኤል ኢራን የኒውክለር ቦምብ ልታመርት ተቃርባለች በሚል ሰበብ በቴህራን የኒውክሌር መሰረተ ልማቶች ላይ እና ወታደራዊ ጣቢያዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እንዲሁም የኢራንን የጦር አዛዦችን እና የኒዉክለር ሳይንቲስቶች ግድያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶችን ፈጽመው እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ በደረሰው ጥቃት የደረሰው የውድመት መጠን በውል ባይታወቅም፣ ማጂድ ታኽት-ራቫንቺም የውድመቱን መጠን ዝርዝር ጥናት ይፋ ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review