በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የተፈጥሮና የሠው ልጅ ቁርኝትን ዳግም የመለሰ ነው ሲሉ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ገለፁ

You are currently viewing በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የተፈጥሮና የሠው ልጅ ቁርኝትን ዳግም የመለሰ ነው ሲሉ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ገለፁ
  • Post category:ልማት

AMN – ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የተፈጥሮ እና የሠው ልጅ ቁርኝትን ዳግም የመለሰ ብቻም ሳይሆን፣ ለመዲናዋ ተጨማሪ ውበት ያጎናፀፈ ነው ሲሉ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ገለፁ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ‘’በመትከል ማንሰራራት’’ በሚል መሪ ሀሳብ 7ኛውን ከተማ አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር አከናውኗል።

የማስጀመሪያ በመርሐ- ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ ዲፕሎማቶች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተለያዩ ባለሞያዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ ባሻገር አሻራቸውን በተግባር የገለጡ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ ተፈጥሮን መንከባከብና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ከእምነት አስተምህሮቱ ባሻገር የሚሰጠው የመንፈስ እርካታ ከፍ ያለ መሆኑን አስረድተዋል።

የሃይማኖት ተቋማት የአካባቢ ስነ ምህዳርን በመጠበቅ ዘመናትን ተሻግረው ዛሬ ላይ ደርሰዋል ወደፊትም ይህ ቀናኢ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥልና ፈጣሪም የሚወደው በጎ ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

አዲስ አበባን ከተቀረው ዓለም እኩል ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ የልማት ስራዎች ለከተማዋ ተጨማሪ እሴትን የሚያጎናፅፉ መሆናቸውን መመልከት እንደቻሉ የሃይማኖት አባቶቹ አስረድተዋል።

ቀደም ብለው ለእይታ የማይማርኩ በካይ ወንዞች ዛሬ ላይ ፀድተው ለብዙዎች የአይን ማረፊያ ከመሆናቸውም በላይ፣ የተፈጥሮና የሠው ልጅ ቁርኝትን ዳግም ያደሰ ስራ ብቻም ሳይሆን የከተማውን ከፍታ የጨመረ ነው ብለዋል።

ህዝቡም ወላጅ ለልጁ እንደሚያደርገው እንክብካቤ ሁሉ የተተከሉ ችግኞች የታለመላቸውን ግብ እንዲያሳኩ በባለቤትነት መንፈስ መንከባከብና ለፅድቀት መጠን መጨመርም ዘላቂ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review