የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሀገራዊ ደህንነት ስጋት ደግኗል ያሉትን ቲክ ቶክን የሚገዙ ባለሀብቶች እንዳሏቸው ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ጉዳዩ የቻይናን መንግስት ይሁንታ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ቻይና ሽያጩን ታፀድቃለች ብለው እንደሚገምቱ ትራምፕ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ የቲክ ቶክን ሽያጭ የሚያስገድደውን ህግ ተግባራዊ ማድረጊያ ጊዜን ለ3ኛ ጊዜ ያራዘሙ ሲሆን፣ በመስከረም 17 የቲክቶክ ባለቤት ኩባንያ የሆነው ባይትዳንስ ወደ ስምምነት መግባት እንደሚጠበቅበት ቢቢሲ ዘግቧል።
ከዚህ ቀደም ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በሂደት ላይ የነበረው ስምምነት ሀገራቱ በታሪፍ ጉዳይ መጎራበጣቸውን ተከትሎ መስተጓጎሉ ይጠቀሳል።
መተግበሪያው የአሜሪካ ተጠቃሚዎችን መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል ስጋት፣ የአሜሪካ ኮንግረስ ባለፈው ዓመት የቲክ ቶክን ሸያጭ የሚያስገድድ ህግ ማውጣቱ ይታወሳል።
በሊያት ካሳሁን