6 ሚሊየን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸው ተገለፀ

You are currently viewing 6 ሚሊየን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸው ተገለፀ

AMN- ሰኔ 23/2017

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በ90 ቀናት ውስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታወቋል፡፡

በኤጀንሲው የኩነትና ነዋሪዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ የፋይዳ መታወቂያ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 6 ሚሊየን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸውን ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያውን በቀላሉ እና በፍጥት እንዲያገኙም አገልግሎቱ በተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው ሰኔ 5 በጀመረው የ90 ቀናት እቅዱ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ለፋይዳ መታወቂያ ለመመዝገብ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ዮሴፍ ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ192 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ አካሂደዋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ 700 የሚደርሱ የፋይዳ መታወቂያ መመዝገቢያ ቴክኖሎጂዎች የሚገኙ ሲሆን የመዲናዋ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉም ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review