ፑቲን እና ማክሮን በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ተወያዩ

You are currently viewing ፑቲን እና ማክሮን በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ተወያዩ

AMN – ሰኔ 25/2017 ዓ.ም

ፑቲን እና ማክሮን በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ በስልክ ተነጋግረዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ከሦስት ዓመታት ወዲህ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ሲመክሩ ይህ የመጀመሪያቸዉ ነዉ፡፡

የማክሮን ጽህፈት ቤት የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ንግግር አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ ፕሬዝዳንት ማክሮን በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ግጭቱን ለማስቆም ድርድር አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ማክሮን በዚሁ ጉዳይ ላይ የዩክሬኑን አቻቸዉን ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ማነጋገራቸውን የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንት ማክሮን የሁለቱን አካላት የስልክ ንግግር ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሳወቃቸውም በዘገባዉ ተጠቅሷል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review