ሁለቱ ቻይናውያን በአሜሪካን ወታደራዊ ማዕረግ ያላቸውን ሰዎች ለስለላ ለመመልመል ሲሞክሩ ተይዘው በኤፍ ቢ አይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የአሜሪካ ፍትሀ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የ38 ዓመቱ ዩዋንስ ቼን እና የ39 ዓመቱ ሊረን ሪያን የቻይና መንግስት ደህንነት ሚኒስቴርን በመወከል ሲሰልሉ ተገኝተዋል ነው የተባለው፡፡
አሜሪካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቻይናውያን ይፈፀምብኛል የምትለውን የስለላ እንቅስቃሴ ለመከላከል የሚያስችላትን ህግ ጠበቅ አድርጋለች፡፡
ቻይና በበኩሏ ይህ ከእውነት የራቀ ተራ ውንጀላ እና ቻይናውያንን በተለየ መልኩ ለማጥቃት አሜሪካ የምታደርገው ጥረት አካል ነው ስትል ውንጀላውን ማስተባበሏን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በወርቅነህ አቢዮ