በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 79 ሺህ 34 ተማሪዎች፣ 95 ከመቶው ሃምሳና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላላም ሙላቱ (ዶ/ር) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 79 ሺህ 34 ተማሪዎች፣ 95 ከመቶው ሃምሳና ከዚያ በላይ ውጤት በማምጣት ወደሚቀጥለው ክፍል ማለፋቸውን ተናግረዋል።
ለውጤቱ መመዝገብም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ዋንኛ አስተዋፅኦ አለው ያሉት ቢሮ ኃላፊው፣ በተለይም የግብአት አቅርቦት፣ የተማሪዎች ምገባ መሳለጥ፣ በሒሳብ እና እንግሊዘኛ ትምህርቶች የተሰጠ ትኩረት እንዲሁም የትምህርት በቴሌቪዥን መጀመር ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።
በአለሙ ኢላላ