በበጀት ዓመቱ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

AMN- ሰኔ 26/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አአባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

የግብርና ምርት እና ምርታመነትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሊታረስ የሚችል ሰፊ መሬት ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግስትም መሬትን በአግባቡ በመጠቀም ለሀገራዊ ዕድገት እያዋለ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት መታረሱን አስታውሰው፣ ዘንድሮ ግን 31.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት መታረሱን አስታውቀዋል፡፡

ይህም ከዓምናው አንጻር 5.8 ሚሊየን ሄክታር ተጨማሪ መሬት መታረሱን አመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከምርት አንፃር አምና ከታረሰው መሬት በሁሉም የሰብል አይነቶች 1.2 ቢሊየን ኩንታል ምርት ሲሰበሰብ ዘንድሮ ደግሞ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

የተገኘው ምርት ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ24.7 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አመላክተዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review