ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ም ሰጥዋል፡፡
በዘንድሮው ዓመት 1.3 ሚሊየን የውጭ ሀጋራት ዜጎች ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደቻሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ 150 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችም መካሄድ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘርፉ ከምንግዜም በላይ የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበት እንደሆነ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የኢሚጊሬሽን ሪፎርም፣ የሆቴል ግንባታ፣የየአየር መንገድ መዘመን፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪስት መዳረሻዎች ግንባታ ለዘርፉ እድገት ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በሚካኤል ህሩይ