የህዳሴ ገድብ ክረምቱ እነዳበቃ እንደሚመረቅ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አአባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
ህዳሴ ግድቡ ክረምቱ ሲያልቅ እንደሚመረቅ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በግድቡ ዙሪያ ግብፅ እና ሱዳን እንዲሁም የተፋሰሱ ሀገራት ስጋት ሊኖራቸው እንደማይገባም አስገንዝበዋል፡፡
የሚመጣው ልማትና ኃይል ለሁሉም ሀገራት የሚተርፍ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ እስከበለጸገችና እስካደገች ድረስ የግብፅ እና የሱዳን ወንድሞቻችንን ጉዳት አንፈልግም ብለዋል፡፡
ለግብፅ ውሃ ይቀንሳል የሚለው ሀሳብ መሰረተቢስ እንደሆነ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣ አስዋን ግድብ አንድም ሊትር ውሃ አይቀንስም ሲሉም አክለዋል፡፡
’’ከዚህ በኋላ ህዳሴ ስጋት ሳይሆን በረከት ነው፤ የተፋሰሱ ሃገራትም ይህን ሊረዱ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀብቱ የሁላችን ነው፣ ንግግር ካስፈለገም ዝግጁ ነን በማለት ተናግረዋል፡፡
’’ህዳሴ ግድብን ክረምቱ እንደወጣ ስናስመርቅ የተፋሰሱ ሀገራት ልንጋብዛቸው እንፈልጋለን በማለትም፣ በዚሁ አጋጣሚም ጥሪ አቀርብላቸዋለው’’ ብለዋል፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ