የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
በፌዴራል መንግስት 20 ገደማ የመስኖ ግድቦች እየተሰሩ እንደሚገኙ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ግድቦቹ ሲጠናቀቁ በአንድ ጊዜ ብቻ ከ 220 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት ይችላሉ ብለዋል፡፡
በግንባታ ላይ ከሚገኙት መካከል 6ቱ እስከ መስከረም ወር ድረስ ተመርቀው አገልግሎት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡
ግድቦቹ በተለያዩ ክልሎች ከ84 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
መንግስት በብዙ ቢሊየን ብሮች ለመስኖ ግንባታ ወጪ የሚያደርግ ሲሆን፣ ምርታማነትን በመጨመር ሂደትም ከፍተኛ አስተዋፅ እያበረከተ እንደሚገኝም ነው ያመላከቱት፡፡
በማሬ ቃጦ