የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉትን አውሮፕላኖች ብዛት ወደ 180 ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአገልግሎት ዘርፉ ከተመዘገቡ እድገቶች እና ውጤቶች መካከል አንዱ ማሳያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
አየር መንገዱ በተያዘው ዓመት ተጨማሪ 13 አውሮፕላኖችን በመግዛት አጠቃላይ የአውሮፕላን ብዛቱ 180 መድረሱን ጠቁመዋል።
ስድስት ተጨማሪ አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ ያላውን የመዳረሻ ብዛት ወደ 136 ማሳደጉን አመልክተዋል።
በተያዘው ዓመት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከ19 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ማጓጓዙንና ይህ ከለውጡ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ገደማ መጨመሩን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ እያገኘ ያለውን ትርፍ ጨምሮ እያስመዘገባቸው ያሉ ስኬቶች በኢትዮጵያ የሚታይ እድገት እንዳለ የሚያመላክት ነው ብለዋል።