በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በህገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ65ሺ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው ከነዳጅ አቅርቦት ስርጭት እና ግብይት ጋር በተያያዘ ከ59 ኩባንያዎች፣ ከ129 ማደያ ባለቤቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ባላቸው አቅም ልክ አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ተጠቃሚዎችን ለወረፋ እና ለእንግልት በመዳረጋቸው 12 ማደያዎች መታሸጋቸውን ተናግረዋል።
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከሐምሌ 1 ጀምሮ በህገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ65ሺ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ያስታወቀው ቢሮው ህገወጥነት በመከላከል ሂደት ውስጥ ከ5.9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገባቱንም አስታውቋል።
በአሸናፊ በላይ