ነዋሪዎቹ የዘንድሮውን የክረምት የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ንኢመተላህ ከበደ በተገኙበት አካሂደዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 7ኛውን ዙር ከተማ አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የዘንድሮውን የክረምት ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አካሂደዋል።
ችግኞችን በመትከል ለትውልድ ተሻጋሪ የአየር ንብረት ያላት ሀገር መፍጠር ከአሁኑ ትውልድ ይጠበቃል ሲሉም ተሳታፌዎቹ ተናግረዋል።
በየዓመቱ በሚከናወን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የነዋሪው ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው ያሉት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ንኢመተላህ ከበደ፣ ችግኞች ከተተከሉ በኋላ መንከባከብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የክፍለ ከተማው ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘየደ ቢወጣ፣ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ከ400 ሺህ በላይ የተለያዩ የጥላ እና ፍራፍሬ ችግኞች ለመትከል መታቀዱን አስታውቀዋል።
በዝናሽ ሞዲ