በመዲናዋ በትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኙ 1 ሺህ 238 አዋኪ ድርጊቶችን ማስወገድ ተችሏል

You are currently viewing በመዲናዋ በትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኙ 1 ሺህ 238 አዋኪ ድርጊቶችን ማስወገድ ተችሏል

AMN- ሰኔ 28/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ በትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኙ 1 ሺህ 238 አዋኪ ድርጊቶችን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ማስወገድ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበሩ አፈጻጸሞችን የግምገማ እና የዕውቅና መድረክ እያከናወነ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፣ በበጀት ዓመቱ በትምህርት አቅራቢያ ይገኙ የነበሩ 1 ሺህ 238 አዋኪ ድርጊቶችን ማስወገድ እንደተቻለ ገልጸዋል።

ይህም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከተከናወነው መሰል ተግባር ጋር ሲደመር 5 ሺህ የሚደርሱ አዋኪ ድርጊቶች ከትምህርት ቤት አቅራቢያ እንዲወገዱ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ከ27 ተቋማት ጋር በቅንጅት መሰራቱን የገለጹት ኃላፊው፣ በቀጣይ ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግረዋል።

በዚህም በ2018 የትምህርት ዘመን ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን በትምህርት ሰዓት የትምህርት ደንብ ልብሶችን ለብሰው በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚዞሩ ተማሪዎችን መያዝ እንዲቻልና ለወላጅ ወይም ለትምህርት ቤቶቻቸው እንዲያስረክብ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።

በበላይሁን ፍሰሀ እና ዓለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review