በዛሬው ዕለት 21 ፕሮጄክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing በዛሬው ዕለት 21 ፕሮጄክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN-ሰኔ 29/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን በአጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “መዲናችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

👉ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣

👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ – በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣

👉ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣

👉 የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣

👉 ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣

👉 ከቂርቆስ ማርገጃ – ቡልጋሪያ፣

👉 ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ – ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣

👉 ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review