አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመኑን የዋጀ ብቁ ሚዲያ ለመሆን የሚያስችሉትን ስራዎች እየሰራ መሆኑን አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመኑን የዋጀ ብቁ ሚዲያ ለመሆን የሚያስችሉትን ስራዎች እየሰራ መሆኑን አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

AMN- ሰኔ 28/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ዘመኑን የዋጀ፣ ለተደራሲያኑ የሚመጥን፣ ከመዲናዋ እድገት ጋር እኩል የሚራመድ፣ ተወዳዳሪ እና ብቁ ሚዲያ ለመሆን የሚያስችሉትን ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ራሱን በቴክኖሎጂ እና በሰው ኃይል በማደራጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገትና ተደራሽነቱን እያሰፋይገኛል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ጠንካራ የስራ ባህልን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘንድ በመፍጠር ለመዲናዋ ፈጣን እድገት መሳለጥ እየተጋ ስለመሆኑ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የትውልድ ድምጽ የሆነው ኤ ኤም ኤን የመዲናዋ እድገትና ለኑሮ ምቹነትን ዋነኛ ትኩረት በማድረግ ቁም ነገር አዘል ዝግጅቶችን በስፋት እያቀረበ ይገኛል፡፡

ወጣቶች በሥራ ተግተው ራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን ሊጠቅሙ እንደሚገባ አጽንዖት የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ተቋማቸው በቅርቡ ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ ሊሰራበት ከስምምነት የደረሰው ‹‹የሚሰሩ እጆች ወግ›› የወጣቱን የሥራ ባህል በማጎልበት ለሚፈለገው ውጤት ተጨማሪ ብርታት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ተቋሙ የጀመረው ትምህርት በቴሌቭዥን ፕሮግራም ስርጭት ሀገሪቱን የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ቀጣይነቷን በማይናወጥ መሰረት ላይ ለማድረስ ያለመችውን ትልም ለማሳካት የተወጠነ መሆኑንም አንስተዋል።

በትውልድ ግንባታ ረገድም ተቋሙ እየሰራቸው ያሉ ሌሎች ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ያብራሩት አቶ ካሳሁን፣ በቀጣይነት በ”አዲስ 24/7” የመረጃ ሰዓት በሳቢ እና አዳዲስ አቀራረቦች ወደ ተመልካቾች ለመድረስ እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review