በአዳማ ከተማ በመንግሥት በጀትና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
የተመረቁ ፕሮጀክቶችም የዶሮና የወተት ላሞች እርባታ ማዕከላት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ህንፃ፣የወረዳ የአስተዳደር ህንፃዎች፣የአስፋልት መንገዶች እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝቡን የመልማት ፍላጎት መሰረት አድርገው የተገነቡ ሲሆን የነዋሪውን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልሱ መሆናቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ፣የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ገዛሊ አባሲመል እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።