የከተማ አስተዳደሩ ለህጻናትና እናቶች አልሚ ምግቦችን ለማቅረብ 518 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን ገለጸ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ ለህጻናትና እናቶች አልሚ ምግቦችን ለማቅረብ 518 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን ገለጸ

AMN – ሰኔ 30/2017 ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩ በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው 2ኛ ዙር የህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ በይፋ ለማስጀመር ድጋፉን ለማቅረብ ውል ከገባው የህብረት ሥራ ኮሚሽን ጋር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተለይም በቀዳማዊ ልጅነት ላይ እየሠራ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ለህጻናትና እናቶች አልሚ ምግቦችን ለማቅረብ ከህብራት ሥራ ማህበራት ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል።

ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ለ2018 ዓ.ም፤ 518 ሚሊዮን ብር በጀት ይዞ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

33 ያህል የህብረት ሥራ ማህበራት ባለፉት ሶስት ዓመታት አልሚ ምግቦችን ለእናቶችና ህጻናት ሲያቀርቡ ቆይተዋል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በቀጣይም አገልግሎቱን ለማጠናከር 55 የህብረት ስራ ማህበራት መመረጣቸውን ተናግረዋል።

በዓለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review