ለሃገሪቱ ሁለንተናዊ እድገትን ለማረጋገጥ እና ለዳበረ ዴሞክራሲዪዊ ስርአት ግንባታ ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል::
ለሲቪክ ማህበራት አባላትና አመራሮች በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዙሪያ በቂረቆስ ክፍለ ከተማ አዳራሽ ስልጠና ተሰጧል::ስልጠናውንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ሰጥተዋል፡፡
በስልጠና መድረኩም የብልፅግና ፖርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻና ምክትል ሀላፊዋ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሺፈራው ተገኝተዋል::
አቶ ሞገስ ባልቻ ለዳበረ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና አገር እድገት መንግስትና ሲቪክ ማህበራት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::ሲቪክ ማህበራቱም በአዲስ አበባ ከተማ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሚደንቅና ከዚህ በፊት በነበሩ መንግስታት ሊሰራ ቀርቶ ፍፁም ያልታሰበ እንደነበር አንስተዋል::
በአዲስ አበባ ብቻ ከ9 ሺህ በላይ የሲቪክ ማህበራት የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በርካታ የመረዳጃ እድሮች ይገኙበታል::የመረዳጃ እድሮች ምክር ቤትም እነዚህን እድሮች ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል::
አቶ ሞገስ ከሲቪክ ማህበራቱ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን መንግስትና ሲቪክ ማህበራቱ በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አውስተው በቀጣይም ተመሳሳይ የስልጠና መድረኮች እንደሚዘጋጁ አሳውቀዋል::
በየሺዋስ ዋለ