ወጣቶችንና ህፃናትን ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎችን መስራት ተገቢ መሆኑን አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ

You are currently viewing ወጣቶችንና ህፃናትን ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎችን መስራት ተገቢ መሆኑን አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN – ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የህፃናት ማቆያና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት የምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ፣ ከስልሳ በመቶ በላይ ነዋሪዎቿ ህፃናትና ወጣቶች በሆኑባት አዲስ አበባ ከተማ፣ የሚሰሩ የልማት ስራዎች እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕከል ያደረጉ መሆን እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ወጣቶችንና ህፃናትን ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎችን በመስራት በኩል ክፍተቶች እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ ጥራቱ፣ አሁን ላይ በህብረተሰቡና በመንግስት ትብብር ወጣቶችንና ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቷም የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያና የህፃናት ማቆያ ማዕከላትን በስፋት እየገነባች እንደምትገኝም አቶ ጥራቱ አንስተዋል።

የሚገነቡ የልማት ማዕከላት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚቀረፁባቸው ስለሆኑ፣ ህብረተሰቡ በባለቤትነት ሊጠብቃቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review