በአውሮፓ የተከሰተዉን ከባድ ሙቀት ተከትሎ በ12 የአውሮፓ ከተሞች ከ2 ሺ 300 ሰዎች በላይ ህይወት መቅጠፉ ተነግሯል፡፡
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2 ባሉት 10 ቀናት በተደረገ ጥናት፣ ከተመዘገቡት 2 ሺ 300 ሞቶች ውስጥ 1 ሺ 500 የሚሆኑት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
ጥናቱ ከዪናይትድ ኪንግደም፣ ኔዘርላንድ፣ ዴንማርክ እና ስዊዘርላንድ በተውጣጡ 5 ተቋማት የተደረገ ሲሆን ለሙቀት መጨመሩ እንደ አንድ ምክንያት ለተጠቀሰው የአየር ንብረት ለውጥ የሰዎች አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክቷል።
ከፍተኛው ሙቀት ቀድሞ የነበረን በሽታ በማባባስ ለሞት የመጋለጥ እድልን ያሰፋ መሆኑንም አልጀዚራ በዘገባው አትቷል።
በሊያት ካሳሁን