በበጀት ዓመቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማሽነሪ እና በብር የተቀናጀ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማሽነሪ እና በብር የተቀናጀ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነታቸውን ከማሳደግ አንፃር ከ4 ሺህ 2 መቶ በላይ የማሽነሪ አቅርቦት እና ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ የተቀናጀ ድጋፍ በማድረግ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤው የበጀት ዓመቱን የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በበጀት ዓመቱ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የድጋፍ ማእቀፍ ተግባራዊ በማድረግም 1 ሺህ 664 ነባር እና ከ400 በላይ አዲስ ስትራቴጂክ ገቢ ምርቶችን ማምረት እንደተቻለም አመልክተዋል፡፡

በውጤቱም 10 ሚሊየን ቶን ተኪ ምርት በማምረት ከ975.1 ሚሊየን በላይ የውጪ ምንዛሪ ማዳን እንደተቻለም አንስተዋል፡፡

ነባር176 እና አዲስ 41 አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቱትን ምርት ወደ ውጪ መላክ መቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከ20 ሺህ 300 በላይ ቶን ምርት በመላክ ከ162.1 ሚሊየን ዶላር በላይ ማስገኘት ተችሏል ብለዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review