የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል በበጀት አመቱ 1ዐዐ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችና 15ዐ ሚኒባሶች መግዛት መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል በበጀት አመቱ 1ዐዐ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችና 15ዐ ሚኒባሶች መግዛት መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም

የከተማ አስተዳደሩ 1ዐዐ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች እና 15ዐ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶችን በመግዛት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል ችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአድዋ ድል መታሰቢያ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጀት ዓመቱን የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የማሻሻል ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡

የብዙሃን ትራንስፖርት በቀን በአማካይ በህዝብ ትራንስፖርት የሚጓጓዝ ህዝብ 3.79 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ ለ4.025 ሚሊየን አገልግሎት መስጠቱን አመላክተዋል፡፡

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል ጋር በተያያዘም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ካሉት 45 ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል 35ቱን በቴክሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከ1.8 ሚሊየን በላይ የተገልጋዮችን ፋይል በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ መልክ በማደራጀት እና አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይን ድካም ማስቀረት እንደተቻለ አንስተዋል፡፡

ለዓመታት ቁጥጥርና ምዘና ሳይደረግባቸው የቆዩ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ እና የተሸከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ በበጀት ዓመቱ ቁጥጥርና ምዘና በማድረግ ጉድለት የተገኘባቸው ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም አብራርተዋል፡፡

ለትራፊክ አደጋ የሚያጋልጡ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች ቁጥጥር በማጠናከር፣ የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን አዲስ ሲስተም በማልማት በድምሩ 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የትራፊክ ቅጣት መፈጸሙንም ገልጸዋል፡፡

ከፓርኪንግ ስራ ጋር በተያያዘ ተቋሙ ያለማውን አዲስ ፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም ተግባራዊ በማድረግ 144 ማህበራት ወደ ስርዓት በማስገባት ከ310 ሺህ በላይ ተሸክርካሪዎች በተዘረጋው ሲስተም እንዲያለፉ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ የተሸከረካሪ ማቆሚያ ቦታዎች የካ ቁጥር 2ን ጨምሮ ወደ አግልግሎት እንዲገቡ መደረጉንም አመላክተዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review