በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ ከ233 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ ከ233 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች፣ በመዲናዋ በበጀት አመቱ ከ233 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ለእቅዱ ስኬት የገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ በመፍጠርና ጠንካራ የክትትል ሥርዓት በመዘርጋቱ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች፣ የዘንድሮው አፈፃፀም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ ከ83.3 ቢሊየን ብር በላይ እድገት ለማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

በተገኘው ገቢም የመዲናዋን የልማት ፍላጎት ወጪ መሸፈንና ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ነዋሪ መደጐም ተችሏል ብለዋል ከንቲባ አዳነች በሪፖርታቸው::

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review