የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምን አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምን አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ

AMN- ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛና የበጀት አመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የከተማዋ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የመዲናዋን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በተለይ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲብራሩ በጠየቁት መሰረት ወ/ሮ ሊዲያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኃላፊዋ በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ሕዝቡን ባለቤት ማድረጋችን ከፍተኛ ለውጥ አምጥቶልናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሕብረተሰቡ በያለበት ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ መደረጉ ትልቅ አጋዥ አቅም ሆኗል በማለት አብራርተዋል፡፡

በከተማዋ የተደራጀው የሰላም ሰራዊትም፣ ለሰላም እና ፀጥታው አስተዋፅኦ አበርክቷል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ፣ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በሦስት ፈረቃ እንዲሰሩ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ የተሰሩ እነዚህ ስራዎች የከተማዋን የወንጀል ምጣኔ በ43 በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡ የተለመደ ተባባሪነቱን እና ተሳትፎውን ይቀጥል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ፣ ቤት አከራዮች የተከራይን ማንነት በሚገባ እንዲያጣሩም አሳስበዋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review