ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

You are currently viewing ምክር ቤቱ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

AMN – ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎዉ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የአስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አቅርበዋል።

ሰብሳቢው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ውሳኔ ፣አስፈላጊነት፣ ዝርዝር ይዘት፣ ተሳትፎ፣ የሚያስገኘው ሃብት፣ የሚፈታው ችግር እንዲሁም ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ያለውን ተገቢነት ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም መሠረት:-

1-በሶስት ዘርፎች ተዋቅሮ የነበረው የአዲስ አበባ የባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፉ የአዲስ አባባ ቱሪዝም ኮሚሽን ሆኖ ለከንቲባ ፅ/ቤት ተጠሪ እንዲሆን፣

2-የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ቢሮን ከትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር ማዋሃድ፣

3-የአዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባባበሪያ ኮሚሽን ጋር ማዋሀድ እና

4-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አንድ ተግባር በከፊል ለውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ማስተላለፍ ላይ የቀረበው ማሻሻያ አዋጅ ምክር ቤቱ በመሉ ድምፅ አፅድቆታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review