የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲዎች ስራዎች አፈፃፀምን መገምገም ጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት የመክፈቻ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ ስኬታማ የስራ አፈፃፀም እና በርካታ ተስፉ ሰጪ ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን አንስተዋል።
በቀበሌ ደረጃ አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ተግባራዊ የተደረገበት ዓመት እንደነበር የጠቀሱት ፕሬዚዳንት ሽመልስ፣ በዚህም ከፍተኛ ውጤት ታይቷል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተስተዋሉ የአፈፃፀም ድክመቶችን ለይቶ በመገምገም እና ለቀጣይ ዕቅድ መነሻ እንዲሆን በማድረግ ለላቀ አፈፃፀም መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑንም ነው ፕሬዚዳንት ሽመልስ የጠቀሱት።
በቡልቻ ነገራ