ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

AMN ሐምሌ 6/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ስም ለሙሃማዱ ቡሃሪ ቤተሰብ፣ ለናይጄሪያ ሕዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።

በዚህ የሀዘን ጊዜ ሀሳባችን ከእናንተ ጋር ነው ሲሉም ገልጸዋል ።

ሙሃማዱ ቡሃሪ ዛሬ እሁድ ከሰአት በኋላ በለንደን በሚገኝ ክሊኒክ ውስጥ በህክምና ላይ እያሉ በ82 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ሲጂቲኤን ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ ቀደም ሲል ዘግቧል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review