ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 170 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚዉሉ ግብአቶችን ድጋፍ ማድረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 170 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚዉሉ ግብአቶችን ድጋፍ ማድረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ሃምሌ 7/2017

ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 170 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚዉሉ ግብአቶችን ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ህይወት አድን ስራ በፈጣሪም በሰዉም ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 170 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 20 የዲያሊሲስ ማሽን እና 10 ዘመናዊ አልጋዎችን በማቅረብ ለ180 ታካሚዎች ለ3 አመት የሚሆን የዳያሊስስ ግብዓቶች ከወንበሮች ጋር አስረክቦናል፡፡

ከፍለዉ መገልገል ለማይችሉ 144 ታማሚዎች በዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና በዳግማዊ ምኒሊክ ኮምፕሬሄነሲቭ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል በየአመቱ እስከ 25 ሚሊዬን ብር በመመደብ የዛሬ አምስት አመት ያስጀመርነዉ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ የዛሬዉ ድጋፍ ሲጨመርበት አገልግሎቱን በእጥፍ ለማሳደግ ስለሚያስችለን ለታካሚዎቻችን ትልቅ እፎይታ ነው።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በህሙማን ፣በከተማ አስተዳደሩ ስም እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እናመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review