በአዲስ አበባ ከተማ በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ

AMN ሃምሌ 08/2017

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4 ዙር ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ (online) ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት በ4 ዙር ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በስኬት ተጠናቋል፡፡

በመዲናዋ በአጠቃላይ ከ50ሺህ በላይ ተማሪዎች በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መዉሰዳቸዉንም ሃላፊዉ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዉ በአራት ዙር ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላትም መስጋና አቅርበዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review