በኒውዮርክ የጣለው ከባድ ዝናብ የከተማዋን የምድር ውስጥ ባቡር በከፊል በጎርፍ ያጥለቀለቀና በርካታ በረራዎችን ያስተጓጎለ መሆኑን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ከባዱ ጎርፍ በኒው ዮርክ እና ኒው ጀርሲ የተከሰተ ሲሆን፣ የምድር ውስጥ ባቡር መስመሮች መጥለቅለቃቸውን እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በተሽከርካሪዎች ውስጥ ተይዘው የቀሩ ሰዎችን ሲረዱ የሚያሳዩ ምስሎች መሰራጨታቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ አስነብቧል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት፣ ከቨርጂኒያ እስከ ፔንሲልቬኒያ ድረስ አሁንም ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሚሆን ከባድ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል አስጠንቅቋል።
በሊያት ካሳሁን