ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በሶስት የተለያዩ ረቅቅ አዋጆች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ነው፡፡
የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ ረቅቅ አዋጅ፣ ነባሩ አዋጅ የነበረበትን ክፍተቶች በሚያርም እና የፖለቲካ ምህዳሩን በሚያሰፋ መልኩ ተሻሽሎ መቅረቡን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ተናግረዋል፡፡
ማሻሻያ አዋጁ ሚዛናዊነትን የጠበቁ ድንጋጌዎችን ያካተተ፣ በቀጣይ የምርጫ ጊዚያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን የሚቀርፍ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያሰፉ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድጉ እንዲሁም የሴቶች የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ የሚያሳድጉ ማሻሻያዎችን ማካተቱንም ቋሚ ኮሚቴው በበጎ እንደተመለከተው በውሳኔ ሃሳቡ ተመላክቷል፡፡

ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ከነባሩ አዋጅ የክልል ምርጫ ጣቢያዎች የቅሬታ አፈታት፣ የምርጫ አደረጃጀት፣ የወጣቶችና ሴቶች ተሳትፎ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ጨምሮ 26 አንቀጾችን ማሻሻሉንም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አብራተዋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም ማሻሻያው ያካተታቸው አንቀጾች የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚጨምሩ የወጣቶችና አካልጉዳተኞችን ተሳትፎ የሚያሳድጉ በመሆናቸው እንዲጸድቁ ሃሳብ ሰጠተጥዋል፡፡
የምክር ቤቴ አባላት ቢሻሻሉ ያሏቸውን ሃሳቦች ካነሱ በኋላም አዋጁ 1394/2017 ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
በፍቃዱ መለሰ