የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸዉን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ 14 አዳዲስ ትምህርትቤቶች ፤ በ64 ነባር ትምህርትቤቶች ላይ ማስፋፋያ የተገነቡ 1655 የማማሪያ ክፍሎች ፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ ምድረጊቢዎችን ፅዱ ፣ ዉብ የማድረግ ፣የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎት ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተተ ነዉ ብለዋል፡፡

ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ስራ አብራችሁን የሰራችሁትን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩኝ እነዚህ ትምህርትቤቶች የእናንተ እና የልጆቻችሁ ሀብት በመሆናቸው እንድትንከባከቧቸው አደራ እላለሁ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡