ፈረንሳይ ከ65 ዓመታት በኋላ በሴኔጋል የሚገኘውን የመጨረሻ ወታደራዊ ሠፈሯን ለሃገሪቱ አስረከበች

You are currently viewing ፈረንሳይ ከ65 ዓመታት በኋላ በሴኔጋል የሚገኘውን የመጨረሻ ወታደራዊ ሠፈሯን ለሃገሪቱ አስረከበች

AMN – ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

በምዕራብ አፍሪካ ፀረ- ፈረንሳይ ስሜቶች መቀስቀሳቸውን ተከትሎ ፈረንሳይ በሴኔጋል የሚገኙትን የመጨረሻዎቹን ሁለት የጦር ሠፈሮች ለሴኔጋል የጦር ሃይሎች አስረክባለች።

የርክክብ ስነ-ስርዓቱ በዋና ከተማዋ ዳካር የተካሄደ ሲሆን የፈረንሳይን የ65 ዓመታት የሴኔጋል ቆይታ እንዲያበቃ አድግሮታል።

ሴኔጋል ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ ከሆነችበት የፈረንጆቹ 1969 ጀምሮ ፈረንሳይ በሃገሪቱ ቋሚ የጦር ሰፈር የነበራት ሲሆን፤ 350 የሚጠጉ የፈረንሳይ ወታደሮች የነበሩበት ጊሌ ካምፕ ለሃገሪቱ የተመለሰ የመጨረሻው የጦር ሰፈር ሆኗል።

የሴኔጋል ፕሬዝደንት ባሲሩ ዲዮማዬ በ2025 ሁሉም የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ አስታውቀው እንደነበር አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል።

ይህ ውሳኔ በርካታ የምዕራብ አፍሪካ የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዢ ሃገራት የፈረንሳይ ወታደሮችን ከግዛቶቻቸው ማስወጣታቸውን እና እንደ ሩሲያ ካሉ ሌሎች የአለም ሃገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከራቸውን ተከትሎ የተደረሰበት እንደሆነም ዘገባው ያመላክታል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review